የተ.አ.ኢ.ፓ

ማብራርያ

ቡልቡላ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓርክ (ቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ) በኦሮሚያ ክልል በላንጋኖና ኣብያታ ስትራተጂካዊ ቦታ መካከል በኢትዮùያ ስምጥ ሸለቆ እምብርት የሚገኝ ፓርክ ሲሆን ፓርኩ በ ኦሮምያ ክልል የኢንዳስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖረሽን ይተዳደራል (www.oipdc.org.et/).

ቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በስሩ ባንክ፤ፖሊስ ጣብያ፤የማሰልጠኛ ማእከል፤ የስራ ኣመራር መሰረተልማቶች የያዘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ፓርኩ ያለበት ቦታና ኣቀማመጥ ሲታይ በዋና የባቡር መስመር፤የፍጥነት መንገድ(ሃዋሳ ሞጆ)፤ኣዲስኣባባ ኣየርፖርት፤ሞጆ ደረቅ ወደብ፤ ኣዲስኣበባ ጁቡቲ ዋናመንገድ ዳር የሚገኝና ደረጃቸው የጠበቁ ሆቴሎችና በኣዳማ ፤ቢሾፍቱ፤ባቱ፤ ሻሸመኔ ሎጆች በቅርበት የሚገኙበት ቦታ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡

ቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በኣገሪቱ ኢኮኖሚ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ፓርክ ሲሆን ይኸውም በድህነት ቅነሳ፤በገጠር ስራ እድል ፈጠራ፤ከግብርና ስራዎች ውጭ ገቢ በማስገኘት፤ ምግብ ነክ ኣግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና በኣጠቃላይ የገጠር ማህበረሰቡ ንሮ ከማሻሻል ኣንፃር ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

በኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉት ጠቃሚ ኣድራሻዎች መጠቀም ይቻላል፤

በ ቡሬ የተ.አ.ኢ.ፓ በ100 ኪ/ሜ ዙርያ 6 የገጠር የሽግግር ማእከላት(ገ.ሽ.ማ የሚገኙ ሲሆኑ እነዚህም ሻሸመኔ፤ዶዶላ፤ሮቤ፤ኢተያ፤ዌለንጪቲ፤ እና መቂ ናቸው፡፡ እነዚህ የገጠር ሽግግር ማእከላት በኢትዮùያ መንግስት ተነሳሽነት ሲቋቋሙ የገጠር ልማቱን ለማሳደግ ብቻ የተቋቋሙ ሳይሆኑ የ ቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ ከኣከባቢው ማህበረሰብ በጥሬ እቃ ኣቅርቦት ለማስተሳሰር ጭምር ታሳቢ በማድረግ የተቋቋሙ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት በገጠር የሽግግር ማእከላት ምርት ከገበሬዎች የመሰብሰብ፤ማጣራት፤መጋዘን ላይ ማከማቸትና ምርት ወደ ሌላ ከመጓጓዙ በፊትም የመጀመርያ ደረጃ የፕሮሰሲንግ ስራ የሚሰራባቸው ማእከላት ናቸው፡፡ ከዚህ ኣንፃር እነዚህ ማእከላት ለኣብዛኛዎቹ የኣከባቢው ኣርሶ ኣደሮች እሴት ሰንሰለት መሰረት ያደረገ የምርት ግብይትና የመገናኛ ማእከላት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

መረጃዎች
ዜናዎች
በቡልቡላ ኢንቨስት አድርጉ

Hello, welcome to Bulbula Integrated Agro Industrial Park, we are the first choice for Asian, European and American foreign investors to invest in Bulbula IAIP…

ኩነቶች
There are currently no events.