የተ.አ.ኢ.ፓ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን (ኢ.ኢ.ኮ) በ1984 ዓ/ም የተቋቋመ ራሱን የቻለ ተቋም ሲሆን ዋና ዓላማውም የግል ኢንቨስትመንት በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለማበረታታት የተቋቋመ ነው፡፡

አጠቃላይ የኮሚሽኑ እንቅስቃሴ በጠ/ሚንስትሩ በሚመራ ቦርድ ክትትል የሚደረግበት ሲሆን ተቋሙም የቦርዱ አባል በሆነ ኮሚሽነር ይመራል፡፡

ኢ.ኢ.ኮ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከመሳብና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ለማዘመን በቅርቡ የመዋቅር ሪፎርም አካሂዷል፡፡

በ ኢ.ኢ.ኮ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያጠቃልላል፤

  • የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት እድሎች በተለይም የውጭ ኢንቨስትመንት ማበረታታትና ማስተዋወቅ
  • የኢንቨስትመንት ፈቃድ፤የንግድ ፈቃድና የኮንስትራክሽን ፈቃድ መስጠት
  • የመግባቢያ ሰነዶች፤የህብረት ስምምነቶችና ማሻሻያዎች ማፅደቅ
  • የንግድ ፈቃድ ሰርተፊኬት መስጠት፤ማደስ፤ማሻሻል፤መተካት ወይም መሰረዝ
  • የንግድ ወይም የተቋም ስም መመዝገብና ማሻሻል እንዲሁም መተካት ወይም መሰረዝ
  • የስራ ፈቃድ መስጠት፤ማደስ፤መተካት፤ማገድ ወይም መሰረዝ
  • ለኣንደኛ ደረጃ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ደረጃ መስጠት
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነቶችና ኤክስፖርት ተኮር የሆኑ በኣገርውስጥና በውጭ ካምፓኒዎች የሚደረጉ ትብብሮች መመዝገብ
  • ከመንግስት እውቅና ሲገኝ ከሌሎች ኣገራት ከኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ዋስትና ከመስጠት ጋር የተያያዙ ድርድሮች ማካሄድና ስምምነቶች መፈፀም
  • ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በፖሊሲ ዙርያ መደረግ ያለበት ማሻሻያ ለመንግስት ማማከር

ከዚህም በተጨማሪ ኢ.ኢ.ኮ ለኢንቨስተሮች ግልጋሎት ኣሰጣጥ በሚመች መልኩ የተቃኘ ነፃና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ኣገልግሎት መስጠት

  • እነዚህ ኣገልግሎቶች(መረጃዎች) በቀጥታ በኮሚሽኑ ድህረገፅ፤በህትመቶች፤ ወይም በቀጥታ የኢንቨስተሮች ጥያቄ በመመለስ የሚሰጡ ሲሆኑ ኣገልግሎቶቹ የየሴክተሩ የኢንቨስትመንት ኣማራጮች፤የንግድ ተቋም ኣመሰራረት ህግና ደንብ፤የስራ ቅጥር መመርያዎች ያጠቃልላሉ
  • ኢንቨስተሮች መሬት፤ውሃ፤መብራት፤ስልክ፤የብድር ኣገልግሎት፤የመኖርያ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ኮሚሽኑ ቀጣይ ድጋፍ ማድረግ

የንግድ ፈቃድ፣የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣የኢንቨስትመንት ማስፋፍያ ፈቃድ፣የግብር ማበረታቻ እና የቀረጥ ነፃ ማበረታቻ https://www.invest-ethiopia.com ለማግኘት በሚፈልጉበት ወቅት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የአንድ ማዕከል ኦንላይን ፖርታልን መጎብኘት ይችላሉ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ለምን አስፈለገ?

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ተመራጭ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነች መምጣትዋ፡፡ በዚህም መሰረት ከአጠቃላይ የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ገቢ ከግማሽ በላይ ከአግሮፕሮሰሲንግ ሴክተር የሚመነጭ መሆኑ እንዲሁም ከ80% በላይ የኤክስፖርት ገቢና 85% የስራ እድል በዚህ ሴክተር የሚሸፈን መሆኑ፡፡    

መንግስት በተለያዩ ክልሎች የተቀናጀ የአግሮ ኢንዳስትርያል ፓርክ ያቋቋመ ሲሆን እነዚህ ፓርኮች ኢንቨስትመንትን ከመሳብና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዳስትሪ ከማሳለጥ አንፃር ሚና የሚኖራቸው ሲሆን እነዚህ ፓርኮች የጥሬ እቃ አቅርቦት፤ምርታማነትን ማሳደግ፤ የአካባቢው የግብርና ምርትና ኢንደስትሪውን በማስተሳሰር አግሮ ፕሮሰሲንግ ሴክተሩ ውጤታማና ቀጣይነት እንዲኖረው ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋል፡፡

ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊት ኢትዮጵያ በ10 ክልሎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረች ስትሆን አጠቃላይ የህዝብ ብዛትዋም 115 ሚልዮን ይደርሳል፡፡ ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ ስትሆን ከአህጉሩም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት አንዷ ናት፡፡

ኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ መሬትና ምቹ የአየር ሁኔታዋ ከውሃና የእርሻ መሬት ሃብትዋ አንፃር ሲታይ አስተማማኝ የኢንቨስትመንት ማዕከል እንድትሆን አስችለዋታል፡፡ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአውሮፓ መካከል መተላለፊያ መንገድ ከመሆነዋ በተጨማሪ ለአፍሪካ ቀንድ ወደብ ያላት ቅርበት ሲታይ ለመካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ገበያዎች ምርትዋን ለማቅረብ የተለየ እድል አላት፡፡

ይህ የመሬት አቀማመጥ በዓለም ላይ ላሉ ላኪዎች ወደር የለሽ የሸንኮራ አገዳ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የአበባ ልማት፣ የደን ልማት (የጎማ ዛፍ ተከላ፣ የፋይበር ተክሎች (ጥጥ፣ ጥድ)፣ የእንስሳት መኖ እና ሌሎች ምርቶች ለመገበያየት የተለየ እድል ይሰጣቸዋል፡፡

የአትዮጵያ አጠቃላይ የመሬት ሽፋን 111.5 ሚሊዮን ሄክታር አካባቢ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 74.3 ሚሊዮን ሄክታር ለግብርና ተስማሚ ነው። በሀገሪቱ 18 ዋና ዋና የአግሮ ኢኮሎጂ ዞኖች ተለይተው ከ3 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለኢንቨስትመንት ቀርቧል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቋና ዘርፈ ብዙ የእርሻ ኢንቨስትመንት እድል ያላት ሀገርም ናት፡፡

በኢትዮጵያ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች (IAIPs) ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ከሚያስችሉ 10 ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ፤

  1. ኢትዮጵያ በአግሮ ኢንዳስትሪ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችል እምቅ አቅም ያላት መሆኑ
  2. ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትና የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ መኖሩ
  3. የኢትዮጵያ መንግስት ለግል ሴክተሩ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑ
  4. ከ 54 ሚልዮን በላይ የሰራተኛ ጉልበት መኖሩና በስልጠና በመደገፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚቻል መሆኑ
  5. ለመካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ያለው ቅርበትና ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ምቹ መሆኑ
  6. ደረጃው የጠበቀ መሰረተ ልማት መኖሩ ለምሳሌ የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መንገድ፤ የመብራት ሃይልና የመንገድ ዝርጋታ
  7. ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ለኢንዳስትሪ ፕሮሰስ የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች ለማቅረብ የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ምርት ያላት ቀዳሚ ሀገር መሆንዋ
  8. ከአፍሪካ አምስተኛዋ ትልቅ የትሮፒካል ፍራፍሬ አምራች ሀገር መሆንዋ
  9. ከኣለም ስድስተኛዋ የእንስሳት ኣምራች ኣገር መሆንዋ
  10. በኣግሮ ኢንዳስትሪ ዘርፍና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት ለሚያደርጉ ሰፊ የማበረታቻ ፓኬጅ የምታቀርብ መሆንዋ
  11. አንፃራዊ በሆነ መልኩ ዝቅተኛ የመብራትና የውሃ ክፍያ መኖሩ  
  12. ከተለያዩ ሀገራት የሁለት ጊዜ የታክስ ክፍያ የማስቀረትና ሌሎች የኢንቨስትመንት ስምምነቶች የፈረመች መሆንዋ
  13. ከጦር መሳርያ ውጭ በሁሉም ሁሉም ምርቶች ለድሃ ሀገራት ከቀረጥ ውጭ ወደ አውሮፓ ህብረት ሃገራት ለማቅረብ የሚፈቅደውን ስምምነት አካል መሆንዋ
  14. አራት መቶ ሚሊዮን ህዝብ ካለው የምስራቅና ደቡብ ኣፍሪካ ሃገራት የጋራ ገበያ ማህበር (COMESA) አባል መሆንዋ
  15. ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ስምምነት አባል በመሆንዋ ኢንቨስተሮች በአፍሪካ በሚያካሂዱት ግብይት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉበት እድል መኖሩ
This is the heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

This is the heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

This is the heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.