ዜናዎች

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለተቋማት፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በመግባት ፈር ቀዳጅ ለሆነው ለሪች ላንድ ባዮ ኬሚካል ፕሮዳክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዕውቅና ተሰጧል።

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ህዳር 17/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ባዘጋጀው የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ በተሟላ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በመግባት ፈር ቀዳጅ ለሆነው ለሪች ላንድ ባዮ ኬሚካል ፕሮዳክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዕውቅና ተሰጧል። ኑ በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ያድርጉ!! የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን።

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ ባለሀብቶች በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነሳሳ መዝሙር በህፃናት አቀርብ።

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ ባለሀብቶች በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነሳሳ መዝሙር በህፃናት ሲቀርብ። ኑ በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ያድርጉ!! የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን።

ውድ ኢንቨስተሮቻችን የመሰረተ ልማቶች በተሟሉለት የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክን ኑ እና በጋራ እናልማ ።

ተዘርዝሮ የማያልቅ የተቀናጁና ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ በ260 ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሲሆን 168 ሄክታር መሬት ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ዝግጁ ተደርጓል።

ቡሬን የተመለከቱ ዜናዎች ባለሃብቶች የማይነጥፍ የግብርና ምርት በሚገኝበት አማራ ክልል መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ጥሪ አስተላለፉ፡፡

ባለሃብቶች የማይነጥፍ የግብርና ምርት በሚገኝበት አማራ ክልል መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ጥሪ አስተላለፉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO የስራ ኃላፊዎች የይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን ፓርኩ ከምስረታው ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በአቅም ግንባታና በቁሳቁስ ሲረዳ መቆየቱ የሚታወስ ነው ፡፡ UNIDO ፓርኩ ድጋፍ በሚያስፈልገው ጉዳዮች ሁሉ ከዚህ ቀደም የሚያደርጋቸውን ድጋፎች በበለጠ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ፡፡ የስራ ኃላፊዎቹ በይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ እየተከናወነ ባለው የስራ እንቅስቃሴ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO የግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ተዘራ የይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ግብርናን በማዘመን የሀገሪቱን የኢኮኖሚን ለማሰደግም ሆነ ለወጣቶች የስራ ፈጠራ እያከናወነ ያለው ተግባር ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ፡፡ የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መምሩ ሞኬ የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚገልጽ ጽሑፍ አቅርበው ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡

1 4 5 6 7