የተ.አ.ኢ.ፓ

የኢትዮጵያ የተ.አ.ኢ.ፓ

የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓረኮች ግብርናን ለማዘመንና የግብርና ግብይትን ለማሳደግ የተቋቋመ የኢኮኖሚ ዞን ነው፡፡ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓረኮች በግብርና ምርት ኣቅርቦት፤የቤት ውስጥ ምርት ማሳደግ፤ትኩረት በሚሰጣቸው ኣዝርእት ፐሮሰሲንግ ፤ ለገበያ የሚውሉ የግብርና ምርቶች፤በምግብ ፕሮሰሲንግ፤ በግብርና ምህንድስናና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ እጅግ ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ኣቅርቦት እንዲሟላለት ተደርጎ የተደራጀ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ነው፡፡

ይህ ድህረገፅ የኣራቱም ኢንዳስትሪ ፓርኮች መረጃ በኣንድ ማእከል ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ድህረገፁ በተባበሩት መንግስታት የኢንዳስትሪ ልማት ድርጅት ድጋፍና በኢትዮጺያ መንግስት ኣዘጋጅነት እንዲሁም በንግድና ኢንዳስትሪ ሚንስትር ኣስፈፃሚነት ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን ኣጠቃላይ ኣላማውም የግሉ ኢንቨስትመንት መሳብ፤ስራ እድል መፍጠር፤የኤክስፖርት ምርት ማሳደግ፤ የከተማና ገጠር ነዋሪዎች ድህነት መቀነስና በኣጠቃላይ የአገሪቱ ግብርና ማዘመን ነው፡፡

ኣገር ኣቀፍ yx!T×ùÃ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓረኮች (ኢ.የተ.ኣ.ኢ.ፓ)

ኣራቱ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓረኮች ዝርዝር

  • ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ ኣማራ ክልል (ሰሜን ምዕራብ)
  • ቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ ኦሮሚያ ክልል (ማእከላዊ)
  • ይርጋኣለም የተ.ኣ.ኢ.ፓ ሲዳማ ክልል (ደቡብ)
  • ባዕኸር የተ.ኣ.ኢ.ፓ ትግራይ ክልል (ሰሜን)

የተ.ኣ.ኢ. ፓ በገጠር የሽግግር ማእከላት (ገ.ሽ.ማ) የሚደገፉ ሲሆኑ በነዚህ ማእከላት ዙርያ የሚመረቱ የግብርና ምርቶች የመሰብሰብና ፕሮሰስ የማድረግ ስራ ይሰራሉ፡፡ የተ.ኣ.ኢ. ፓ እና ገ.ሽ.ማ የተለየ የሚያደርጋቸው ለነዚህ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ የሆኑ መሰረት ልማቶች፤መስመሮችና ኣገልግለቶች በተቀናጀ ኣግባብ የሚቀርቡ መሆናቸው ነው፡፡

የኣራቱ ክልሎች ኢንዳስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖረሽኖች (ክኢፕልኮ) ተጠሪነታቸው ለክልሉ ቦርድ ሲሆን በክልላቸው ላሉት የተ.ኣ.ኢ. ፓ እና ገ.ሽ.ማ የማልማትና መሰረተ ልማቶች የማስተዳደር ሓላፊነት ኣላቸው፡፡

የተ.ኣ.ኢ. ፓ መሰረተልማቶችና ኣገልግሎቶች በሚመለከት

ሌሎች የግል ተቋማት ከተ.ኣ.ኢ.ፓ በመተባበር መሰረተ ልማቶችን በመዘርጋት፤ እቃዎችን በጅምላ በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ስልጠናና የኤክስተንሽን ኣገልገሎት በጋራ በመስጠት የላቀ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጺያ የተ.ኣ.ኢ.ፓች ነፃ የሆነ የማምረቻ ቦታና ዘመናዊ የመሰረተልማት ኣቅርቦት ይኖራቸዋል፡፡ ኣጠቃላይ የመሰረተ ልማት ኣገልግሎት የሚያጠቃልላቸው ኣገልግሎቶች ሲታይ የመንገድ፤ የመብራት፤ የስልክ፤ የጎርፍ ማስወገጃ፤የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃና የቆሻሻ ማከሚያ ፕላንት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልዩ የመሰረተ ልማት ኣቅርቦት ፓኬጅ የሚያቀርባቸው ኣገልግሎቶች ሲታይ የማቀዝቀዣ መጋዝን፤የበሽታ መቆጣጠርያ ኣገልግሎት፤የጥራት ቁጥጥር ላቦላቶሪ ፤የጥራት ማረጋገጫ ማእከል፤የጥሬ እቃ መጋዘንና የተማከለ የማምረቻ ማእከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እያንዳንዱ የተ.ኣ.ኢ.ፓ ከኣከባቢያቸው የገጠር ሽግግር ማእከላት (ገ.ሽ.ማ)ና ከኣምራቾች የተሳሰሩ ሲሆኑ በዚህም መሰረት በ100 ኪ/ሜ ዙርያ የሚገኙ 28 የገጠር ሽግግር ማእከላት( ገ.ሽ.ማ) ለያንዳነዱ የተ.ኣ.ኢ.ፓ የግብርና ጥሬ እቃ በማቅረብ ያገለግላሉ፡፡ የገጠር ግብርና ሽግግር ማእከላት ከሚያጠቃልሉዋቸው እገልግሎቶች ውስጥ የጥሬ እቃ መጋዝኖች፤ጥሬ እቃ ኣቅርቦት፤የምርት ልየታ፤የምርት ደረጃ ፍረጃ፤የኤክስተንሽን ኣገልግሎት፤የመጀመርያ ደረጃ ፕሮሰሲንግና የማይክሮፋይናንስ ኣቅርቦት ይገኙበታል፡፡

የኣርሶ ኣደሩ ምርትና ምርታማነት በመጨመር ጥሬ እቃ በሚፈለገው መጠንና ጥራት ለተ.ኣ.ኢ.ፓ ለማቅረብ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ቅንጅት ኣስፈላጊ ነው፡፡

የተ.ኣ.ኢ. ፓ የኢንቨስትመንት እድሎች

በፓርኩ የተለያዩ የኣግሮ ኢንድስትሪ ፕሮሰሲንግ የኢንቨስትመንት እድሎች ያሉ ሲሆኑ እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፤

  • ፍራፍሬና ጭማቂ
  • እሽግ የቲማቲም ምርት
  • ሃይል ሰጪ ምርቶች(ስታርች)
  • ቡናና ሻሂ
  • ተዘጋጅተው የታሸጉ ኣትክልቶች
  • የቅመማቅመም ዱቄትና ዘይት
  • ቅመማቅመም ደረጃ ፍረጃና ማሸግ
  • ከእፀዋት ዘይት ማምረት
  • ከእፀዋት መድሃኒት ማምረት
  • ከኣትክልት ዘይት ማምረት
  • ዳቦና ኬክ መጋገር
  • ሃይል ሰጪ ምግቦች ማምረት
  • ዱቄት መፍጨት
  • ሌሎች
This is the heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

This is the heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

This is the heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, luctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.