የተ.አ.ኢ.ፓ

ማብራርያ

ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በምእራብ ኢትዮዮùያ ፤ በአማራ ክልል፤በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ የሚገኝ ፓርክ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ411ኪ/ሜ ከባህርዳር ደግሞ በ156 ከ/ሜ በስተ ደቡብ ምዕራብ ይገኛል አማራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን.


ቡሬ የሚገኘው በወለጋ፤ጎንደርና ሽዋ በሚያገናኝ አማካይ መንገድ በመሆኑ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ የሚያስችል ሰፊ እድል ያለው ፓርክ ነው ፡፡ ቡሬ የተ.አ.ኢ.ፓ በ 260.5 ሄ/ር መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን በመጀመርያው ምእራፍም የተሟላ የውሃ፤መብራት፤ስልክና መንገድ፤ የተዘረጋለት ሲሆን ከዚህም በተጭማሪ ለቢሮ፤የሰራተኞች መኖርያና ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የሼድ አገልግሎት ተሟልቶለታል፡፡


በ ቡሬ የተ.አ.ኢ.ፓ በ100 ኪ/ሜ ዙርያ 7 የገጠር ሽግግር ማእከላት (ገ.ሽ.ማ) የሚገኙ ሲሆኑ እነዚህም መራዊ፤ፍኖተሰላም፤ዳንግላ፤እንጅባራ፤ ቻግኒ፤ አማኑኤልና ሞጣ ናቸው፡፡ እነዚህ የገጠር ሽግግር ማእከላት በኢትዮጵያ መንግስት ተነሳሽነት ሲቋቋሙ የገጠር ልማቱን ለማሳደግ ብቻ የተቋቋሙ ሳይሆኑ የ ቡሬ የተ.አ.ኢ.ፓ ከአካባቢው ማህበረሰብ በጥሬ እቃ አቅርቦት ለማስተሳሰር ጭምር ታሳቢ በማድረግ የተቋቋሙ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት በገጠር የሽግግር ማእከላት ምርት ከገበሬዎች የመሰብሰብ፤ማጣራት፤መጋዘን ላይ ማከማቸትና ምርት ወደ ሌላ ከመጓጓዙ በፊትም የመጀመርያ ደረጃ የፕሮሰሲንግ ስራ የሚሰራባቸው ማእከላት ናቸው፡፡ ከዚህ ኣንፃር እነዚህ ማእከላት ለአብዛኛዎቹ የአካባቢው አርሶ አደሮች እሴት ሰንሰለት መሰረት ያደረገ የምርት ግብይትና የመገናኛ ማእከላት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

መረጃዎች
ዜናዎች
የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለተቋማት፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በመግባት ፈር ቀዳጅ ለሆነው ለሪች ላንድ ባዮ ኬሚካል ፕሮዳክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዕውቅና ተሰጧል።

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ህዳር 17/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ባዘጋጀው የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ በተሟላ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በመግባት ፈር ቀዳጅ ለሆነው ለሪች ላንድ ባዮ ኬሚካል ፕሮዳክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዕውቅና ተሰጧል። ኑ በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ያድርጉ!! የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን።

ኩነቶች
There are currently no events.