የተ.አ.ኢ.ፓ

ቡልቡላ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ ምረቃ

ቀን፤ ግንቦት 1/ 2013

የኢትዮùያ መንግስት የኣገሪቱ ግብርና ለማዘመን ቀጣይነት ያለው ስራ እየሰራ ሲሆን ዛሬ ቡልቡላ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ በክቡር ጠቀላይ ሚንሰትር ኣብይ ኣህመድ ተመርቀዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሽዋ በሚገኘው የፓርክ የምረቃ ስነስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ ኣህመድ ባደረጉት ንግግር’’ ግብርናን ለማዘመን የምናደርገው ጥረት ኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርኮችን በመገንባት የበለጠ ኣቅም መፍጠር ይቻላል’’ ሲሉ መልእክት ኣስተላልፈዋል፡፡ ከዛ በመቀጠልም’’

የቡልቡላ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓርክ ምረቃ መንግስታችን ግብርና ፤ገበሬዎችና ሸማቾች ወደ ብልፅግና ለማሸጋገር የያዘውን ራእይ እውን እየሆነ መሆኑ እንደማሳያ ሊወሰድ የሚችል ስራ ነው’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ ገልፀዋል፡፡

የምስራቅ ኣፍሪካ ሃገራት የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርክን (የተ.ኣ.ኢ.ፓ) በማሳደግ ኢንዳስትሪ መር ወደ ሆነው ኢኮኖሚ ለመሸጋገር መዋቅራዊ ሽግግሩን በማፍጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

ቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በ271 ሄ/ር የተገነባ በኣግሮ ፕሮሰሲንግ ትኩረት ያደረገ መንግስታዊ የተ.ኣ.ኢ.ፓ ሲሆን ለዚህ ግንባታ 9 ቢልዮን ብር ወጥቶበታል፡፡

ይህ ፓርክ ከኣቀማመጡ ኣንፃር ከሌሎች ፓርኮች ሲነፃፀር ልዩ እንደሆነ የኢንዳስትሪ ሚንስትሩ ክቡር ኣቶ መላኩ ኣለበል ገልፀዋል፡፡

ፓርኩ በዝዋይ፤ኣብያታና ላንጋኖ ሃይቆች የተከበበ መሆኑና በኣቅራብያው

የባቡር መስመር፤የፍጥነት መንገድ፤ሞጆ ደረቅ ወደብና ለኣዲስኣበባ ቅርብ መሆኑ እንዲሁም ያለምንም ውጣውረድ በቅርበት የእርሻ ጥሬ እቃ ከማግኘትና የኣከባቢው ኣርሶኣደሮች ከመደገፍ ኣንፃር ያለው ኣመችነት ሲታይ የተለየ እንደሚያደርገው ሚንስትሩ ኣክለው ገልፀዋል ፡፡

ምንጭ፤: https://ethiopianmonitor.com/2021/05/09/bulbula-integrated-agro-industry-park-inaugurated/

ዜናዎች
በቡልቡላ ኢንቨስት አድርጉ

Hello, welcome to Bulbula Integrated Agro Industrial Park, we are the first choice for Asian, European and American foreign investors to invest in Bulbula IAIP…

ቡልቡላ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ ምረቃ

ቀን፤ ግንቦት 1/ 2013 የኢትዮùያ መንግስት የኣገሪቱ ግብርና ለማዘመን ቀጣይነት ያለው ስራ እየሰራ ሲሆን ዛሬ ቡልቡላ የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ በክቡር ጠቀላይ ሚንሰትር ኣብይ ኣህመድ ተመርቀዋል፡፡