ማብራርያ
ባዕኸር የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትረያል ፓርክ (ባዕኸር የተ.ኣ.ኢ.ፓ) በባዕኸር ከተማ ኣስተዳደር፤ቃፍታ ሑመራ ወረዳ፤ በምዕራባዊ ዞን ትግራይ ክልል የሚገኝ ፓርክ ሲሆን በትግራይ ክልል የኢንዳስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፐረሽን ስር የሚተዳደር ተቋም ነው (ት.ክ.ኢ.ፓ.ል.ኮ)፡፡
በባዕኸር የተ.ኣ.ኢ.ፓ የውሃ ኣገልግሎት፤የኤለክትሪክ ሃይል መሰረተ ልማት፤የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦይ፤የውስጥ ለውስጥ መንገድና መጋዘን የያዘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የጥራት ቁጥጥር መገልገያዎች፤ የጥራት ማረጋገጫ፤ የስልጠና ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ መሳርያዎች የያዘ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከዋናው የፕሮሰሲንግ ቦታ ውጭ የመኖርያ ቦታ፤ት/ቤት፤የእምነት ተቋምና የንግድ ቦታዎች ያጠቃለለ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ከጠቅላላው የመሬት ስፋት 15% የሚሆነውን ቦታ ለኣረንጋዴ ልማት መጠባበቅያ የተከለለ ነው፡፡
በ ቡሬ የተ.አ.ኢ.ፓ በ100 ኪ/ሜ ዙርያ 7 የገጠር ሽግግር ማእከላት (ገ.ሽ.ማ) ያሉ ሲሆኑ እነዚህም፤ ማይካድራ፤ሰቲት ሑመራ፤ ዓዲጎሹ፤ ኣዲሕርዲ፤ ማይጋባ፤ ዳንሻና ሽረ እንዳስላሰ ናቸው፡፡ እነዚህ የገጠር ማእከላት በኢትዮጺያ መንግስት ሲቋቋሙ የገጠር ልማት ለማሳለጥ ብቻ ሳይሆን የባዕኸር የተ.ኣ.ኢ.ፓ በጥሬ እቃ ኣቅርቦትና ሌሎች ኣገልግሎቶች ለማስተሳሰር ታስቦ የተቋቋሙ ተቋማት ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት በነዚህ የገጠር ማእከላት ከሚሰጡ ኣገልግሎቶች ውስጥ በኣከባቢው የተመረቱ ምርቶች መሰብሰብ፤ ምርት ማጣራት፤ምርት ማከማቸትና ምርት ወደ ሌላ ከመላኩ በፊት ውሱን የፕሮሰሲነግ ስራ የሚሰራባቸው ማእከላት ናቸው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በዙርያው ለሚገኙ ኣብዛኛዎቹ ገበሬዎች የግብርና እሴት ሰንሰለት መሰረት ያደረገ የግብይት ማእከልና መገናኛ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፤፤
UNIDO-AICS Cooperation
Operationalization and Sustainability of IAIPs in Ethiopia (OS-IAIP) Project Factsheet