Regional Investment Promotion Workshops

ኩነቶች

233 233 people viewed this event.

የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓርክ ስራ እድል ከመፍጠር ኣንፃር፤ የውጭ ምንዛሪን ከማመንጨት፤ከግብርና ወደ ኢንዳስትሪ በማሸጋጋርና በኣጠቃላይ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከማረጋገጥ ኣንፃር ያለው ጠቀሜታ ታሳቢ በማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ ኣንፃር የተቀናጀ ኣግሮ ኢንዳስትርያል ፓርኮችና(የተ.ኣ.ኢ.ፓ) የገጠር የሽግግር ማእከላት(ገ.ሽ.ማ) ግብርናውን ገበያ መር በማድረግ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር በማምጣት ረገድ ቁልፍ መሳርያ ሆነው እንደሚያገለግሉ ይታመናል፡፡

ከዚህ ኣንፃር ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ እና 7 የገጠር የሽግግር ማእከላት በኣማራ ክልል የተገነባ ሲሆን ይህ ፓርክ በርካታ የኣገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች የመሳብ ኣቅም እንዳለው ይታመናል፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ የተወሰኑ ባለሃብቶች በፓርኩ ኢንቨስት ለማድረግ ተመዝግበው ቦታ ወስደው ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን በዚህም መሰርት ለፋብሪካ የሚሆን የሼድ ግንባታ በመገንባትና ከኢንዳስትሪያቸው ፍላጎት ኣንፃር የኣከባቢውን የግብርና ምርት ለማሳደግ የተለያዩ የኤክስተንሽን ስራ መስራት የጀመሩበት ሁኔታ ኣለ፡፡

በፓርኩና ከፓርኩ ተያያዥነት ባላቸው የኢንቨስትመንት እድሎች ለኣገር ውስጥና ለውጭ ኣገር ኢንቨስተሮች በኣግባቡ በማስተዋወቅ ጥራትና ብዛት ያላቸው ኢንቨስተሮች ለመሳብ የሚያስችል ስራ መስራት ኣስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በክልል ደረጃ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ፎረም በማካሄድ ኢንቨስተሮች በፓርኩ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች፤ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ፓኬጆች፤የመሰረተ ልማት ኣቅርቦትና የግልጋሎት ኣአሰጣጥ ሂደት ምን እንደሚመስል ለማስተዋወቅ እቅድ የተያዘ ሲሆን ይህ የፕሮመሽን ፎረም በፓርኩ የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት በማቀላጠፍና ለገጠር የሽግግር ማእከላት የሚደረገውን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንደሚያሻሽለው ይታመናል፡፡

To register for this event please visit the following URL:

 

ቀንና ሰዓት

2022-04-01 @ 08:00 AM to
2022-04-30 @ 05:00 PM
 

Event Category

Share With Friends