የተ.አ.ኢ.ፓ

ዜናዎች

Yirgalem News Baeker News Bulbula News Bure News News
የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO የስራ ኃላፊዎች የይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን ፓርኩ ከምስረታው ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በአቅም ግንባታና በቁሳቁስ ሲረዳ መቆየቱ የሚታወስ ነው ፡፡ UNIDO ፓርኩ ድጋፍ በሚያስፈልገው ጉዳዮች ሁሉ ከዚህ ቀደም የሚያደርጋቸውን ድጋፎች በበለጠ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ፡፡ የስራ ኃላፊዎቹ በይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ እየተከናወነ ባለው የስራ እንቅስቃሴ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት /UNIDO የግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ተዘራ የይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ግብርናን በማዘመን የሀገሪቱን የኢኮኖሚን ለማሰደግም ሆነ ለወጣቶች የስራ ፈጠራ እያከናወነ ያለው ተግባር ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ፡፡ የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መምሩ ሞኬ የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚገልጽ ጽሑፍ አቅርበው ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡

1 2 3