ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ ኣህመድ በኣማራ ክልል የሚገኘው የቡሬ የተቀናጀ የኣገሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ መረቁ

ቀን፤ ጥር 30/2013

ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ ኣህመድ በኣማራ ክልል የሚገኘው የቡሬ የተቀናጀ የኣገሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ(የተ.ኣ.ኢ.ፓ) መረቁ

ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ የተቀናጀ የኣግሮ ኢንዳስትሪ ፓርክ ልማት ቅድሚያ ከሚሰጡዋቸው ኣጀንዳዎች ኣንዱ ና ዋናው መሆኑ ገለፁ፡፡ በንግግራቸው ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በመፅሃፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰው እየሱስ ክርስቶስ በቃና ላይ በተደረገው ድግስ ውሃን ወደ ወይን በመቀየር ተኣምር እንዳሳየ ሁሉ ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓም የግብርና ምርቶችን ወደውጭ ኤክስፖርት በማድረግና ብልፅግናን በማረጋገጥ የኢትዮùያ ቃና መሆንዋን ማረጋገጥ ኣለባት ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ የተባበሩት መንግስታት የኢንዳስትር ልማት ድርጅት የኢንደስትሪ ፓርኩን በማቋቋም ሂደት መንግስት መደገፋቸውን ኣመስግነዋል፡፡ ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ ከኣራቱ ፓርኮች ኣንዱ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ የተባበሩት መንግስታት የኢንዳስትሪ ልማት ድርጅትም እነዚህ ፓርኮች ከዲዛይንና እቅድ ዝግጅት፤ዝርዝር የኣወጭነት ጥናት ማካሄድ፤የማህበራዊና ኣከባቢያዊ ተፅእኖ ጥናት፤ዝርዝር የምህንድስና ዲዛይንና የክልሉ የኢንዳስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖረሽን ኣቅም መገንባት ላይ ሰፊ ቴክኒካዊ ድጋፍ ኣድርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኣገራዊ የቅንጅት ፕሮገራም(ኣ.ቅ.ፕ) በሚባል ፕሮጀክት ሃብት በማሰባሰብናየኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን በማካሄድ ድጋፍ ኣድርገዋል፡፡

በምረቃው ስነስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆኑ እነዚህም ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮነን፤የኣማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኣገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች ተሳትፈዋል፡፡

ቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በ 260.5 ሄ/ር መሬት የተገነባ ሲሆን ለግንባታውም 165 ሚልዮን የኣሜሪካን ዶላር ወጥቶበታል፡፡ ፓርኩ የተሟላ የውሃ፤መብራት፤ስልክ፤መንገድ፤ቢሮ፤የማምረቻ ሼድና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ተማልተውለታል፡፡ በዚህም መሰረት ፓርኩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ካሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ውስጥ የምግብ ዘይት ማምረት፤በቆሎ፤ኣኩሪ ኣተር፤ማር፤ወተት፤ስጋ፤እንቁላልና ስጋ ፕሮሰስ ማድረግና ኣበባ ማምረት ሲሆን በኣሁኑ ወቅትም በፓርኩ የውጭ ኢንቨስተሮችን ጨምሮ 15 ባለሃብቶች ከክልሉ የኢንዳስትሪ ልማት ፓኮች ኮርፖረሽን ጋር ውል የገቡ ሲሆን በተለያየ የስራ ደረጃም ይገኛሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኢንዳስትሪ ልማት ድርጅት ሃገራዊ የትብብር ፕሮግራም(ሃ.ት.ፕ) በሚል ማእቀፍ ከሌሎች ባለድርሻ ኣካለት ጋር ማለትም ከ FAO,AFDB,EU,AICS እና BMZ በመተባበር ለተ.ኣ.ኢ.ፓ ከጥናት ጀምሮ እስከ ትግበራ ድጋፍ ኣድረገዋል፡፡

ከቡሬ የተ.ኣ.ኢ.ፓ በተጨማሪ በሚቀጥሉት ወራት ሌሎች 3 የተ.ኣ.ኢ.ፓ የሚመረቁ ሲሆኑ እነዚህም መኦሮሚያ የቡልቡላ የተ.ኣ.ኢ.ፓ፤ በሲዳማ ይርጋኣለም የተ.ኣ.ኢ.ፓ እና በትግራይ የባዕኸር የተ.ኣ.ኢ.ፓ ናቸው፡፡ ይህ የተጀመረው የተ.ኣ.ኢ.ፓ እቅድ ኣገራችን የያዘችው የኢኮኖሚ የመዋቅራዊ ሽግግር ከማቀላጠፍ ባሻገር ኢትዮùያ በ 2025 በቀላል የማኑፋክቸሪንግ ኢንዳስትሪ የኣፍሪካ ማእከል ለማድረግ የተያዘውን ራእይ እንደሚያሳካ ይታመናል፡፡

ምንጭ፤ https://www.unido.org/news/ethiopia-prime-minister-abiy-ahmed-inaugurates-bure-integrated-agro-industrial-park-amhara-state

ዜናዎች
የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለተቋማት፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በመግባት ፈር ቀዳጅ ለሆነው ለሪች ላንድ ባዮ ኬሚካል ፕሮዳክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዕውቅና ተሰጧል።

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ህዳር 17/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ባዘጋጀው የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ በተሟላ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በመግባት ፈር ቀዳጅ ለሆነው ለሪች ላንድ ባዮ ኬሚካል ፕሮዳክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዕውቅና ተሰጧል። ኑ በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ያድርጉ!! የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን።

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ ባለሀብቶች በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነሳሳ መዝሙር በህፃናት አቀርብ።

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ የማስተዋወቅና ባለሀብቶችን የመሳብ ታላቅ ፎረም ላይ ባለሀብቶች በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነሳሳ መዝሙር በህፃናት ሲቀርብ። ኑ በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ያድርጉ!! የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን።

ውድ ኢንቨስተሮቻችን የመሰረተ ልማቶች በተሟሉለት የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክን ኑ እና በጋራ እናልማ ።

ተዘርዝሮ የማያልቅ የተቀናጁና ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት የቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ በ260 ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሲሆን 168 ሄክታር መሬት ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ዝግጁ ተደርጓል።